የአሜሪካ እና ሩሲያ ንግግሮች መሬት ላይ ባለው የዩክሬን ነባራዊ ሁኔታ ይመሠረታሉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአሜሪካ እና ሩሲያ ንግግሮች መሬት ላይ ባለው የዩክሬን ነባራዊ ሁኔታ ይመሠረታሉ
የአሜሪካ እና ሩሲያ ንግግሮች መሬት ላይ ባለው የዩክሬን ነባራዊ ሁኔታ ይመሠረታሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.08.2025
ሰብስክራይብ

የአሜሪካ እና ሩሲያ ንግግሮች መሬት ላይ ባለው የዩክሬን ነባራዊ ሁኔታ ይመሠረታሉ

“ቻሶቭ ያርን መያዝ እና በክራስኖአርሜይስክ አቅጣጫ መገስገስ ለፑቲን የጦር ሜዳ የበላይነቱን በመስጠት በድርድሩ ጥንካሬያቸውን ለማሳያት ሊጠቀሙበት ይችላሉ” ሲሉ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ፓሪስ የዓለም አቀፍ እና ንጽጽራዊ የፖለቲካ ትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር እና ሊቀመንበር ሃል ጋርድነር ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ተንታኙ ሩሲያ የልዩ ወታደራዊ ዘመቻ መሠረታዊ ግቦቿን፤ ዶንባስ፣ ዛፖሮዥዬ እና ሄርሶን ክልሎችን ሙሉ በሙሉ ነጻ እስክታወጣ እና የክራይሚያን ደህንነት እስክታረጋግጥ ድረስ፤ ማንኛውንም የተኩስ አቁም ስምምነት እንደማትቀበል ጠቁመዋል።

ጋርድነር “በተለይ የሩሲያ ወታደሮች እየገፉ ባሉበት ወቅት፤ ፑቲን ትራምፕ ለመገናኘት ፈቃደኛ በመሆናቸው ብቻ አቋማቸውን ያለሳልሳሉ ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር ነው” ብለዋል።

ትራምፕ ምን ሊያቀርቡ ይችላሉ?

▪ የአሜሪካን ማዕቀቦችን በደረጃ ማንሳት።

▪ የኔቶን ወደ ዩክሬን መስፋፋት ማስቆም።

▪ ዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪዎች ለሚያረጋግጡት የተኩስ አቁም፤ አዲስ የአውሮፓ የደህንነት ማዕቀፍ ንግግር መጀመር።

የንግግሮቹ ትኩረት ምን ይሆናል?

ጋርድነር “ንግግሮቹ በዋነኛነት በዩክሬን ላይ የሚያተኩሩ ይሆናሉ፤ ነገር ግን ወደ ሰፊ የደህንነት መዋቅር፣ ከኒው ስታርት በኋላ ስላለው የጦር መሳሪያ ቁጥጥር እና የመካከለኛ ርቀት የኒውክሌር ኃይል (አይኤንኤፍ) ስምምነት መፍረስ እንዲሁም ወደ ተጽዕኖ ክልሎች ሊሰፋ ይችላል” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0