ኢራን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአርሜኒያ ኮሪደር መተላለፊያ ልማት ስምምነት ላይ ተቃውሞ እንዳላት የጠቅላይ መሪው አማካሪ ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢራን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአርሜኒያ ኮሪደር መተላለፊያ ልማት ስምምነት ላይ ተቃውሞ እንዳላት የጠቅላይ መሪው አማካሪ ገለፁ
ኢራን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአርሜኒያ ኮሪደር መተላለፊያ ልማት ስምምነት ላይ ተቃውሞ እንዳላት የጠቅላይ መሪው አማካሪ ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.08.2025
ሰብስክራይብ

ኢራን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአርሜኒያ ኮሪደር መተላለፊያ ልማት ስምምነት ላይ ተቃውሞ እንዳላት የጠቅላይ መሪው አማካሪ ገለፁ

የኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሚኒ አማካሪ አሊ አክባር ቬላያቲ፤ “ቀጣናውን የተመለከቱ ስሌቶች እና ስምምነቶች በአዘርባጃን እና አርሜኒያ ብቻ የተገደቡ አይደሉም። የክልሉ የጂኦፖለቲካ ለውጦች፤ የኢራን ድንበር አቅጣጫንም ይቀይራሉ። በዚህም ጥቅማችንን በቆራጥነት የመከላከል መብት አለን” ሲሉ መናገራቸውን የኢራን ዜና ወኪል ታስኒም ዘግቧል።

ቬላያቲ አክለውም፤ የኮሪደር ዕቅዱ ትግበራ የደቡብ ካውካሰስን ደህንነት ለአደጋ ያጋልጣል ብለዋል።

“ኢራን ከሩሲያም ጋር ሆነ፤ ያለ ሩሲያ በደቡብ ካውካሰስ የደህንነት ሁኔታ ላይ ተመስርታ እንደምትንቀሳቀስ ታስረግጣለች። ሩሲያም ከስትራቴጂያዊ እይታ አንፃር ኮሪደሩን እንደምትቃወም እናምናለን” ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0