የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዝዳንት የቀብር ክርክር ተባባሰ - የቤተሰባቸውን ይግባኝ ተከትሎ አስከሬኑን ወደ ሉሳካ የመመለሱ ሂደት ታገደ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዝዳንት የቀብር ክርክር ተባባሰ - የቤተሰባቸውን ይግባኝ ተከትሎ አስከሬኑን ወደ ሉሳካ የመመለሱ ሂደት ታገደ
የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዝዳንት የቀብር ክርክር ተባባሰ - የቤተሰባቸውን ይግባኝ ተከትሎ አስከሬኑን ወደ ሉሳካ የመመለሱ ሂደት ታገደ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.08.2025
ሰብስክራይብ

የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዝዳንት የቀብር ክርክር ተባባሰ - የቤተሰባቸውን ይግባኝ ተከትሎ አስከሬኑን ወደ ሉሳካ የመመለሱ ሂደት ታገደ

የኤድጋር ሉንጉ ቤተሰቦች ከዛምቢያ ጋር አስከሬኑን ወደ ሀገር ለመመለስ ስምምነት ላይ እንዳልደረሱ በመግለጽ የደቡብ አፍሪካን ፍርድ ቤት ውሳኔ ተቃውመው ይግባኝ ጠይቀዋል።

የዛምቢያ እና የሉንጉ ቤተሰብ የፍርድ ቤት ክርክር ዝርዝር፦

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ በደቡብ አፍሪካ ለህክምና ክትትል በሄዱበት ግንቦት 28 ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የዛምቢያ መንግሥትም በሉሳካ ብሔራዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የፕሬዝዳንቱ ቤተሰቦች አስከሬኑን ሰኔ 11 ቀን ወደ ሀገር ለመመለስ መጀመሪያ ተስማምተው የነበረ ቢሆንም፤ አስከሬኑን ወደ ሀገር በሚመለስበት ቀን ግን ስምምነቱን በመሻር፤ በደቡብ አፍሪካ ለመቅበር መወሰናቸውን ጉዳዩን የያዙት ዳኛ ተናግረዋል።

ዛምቢያ ስምምነቱ እንዲከበር በፕሪቶሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማመልከቻ አቅርባ አሸንፋለች። ፍርድ ቤቱ ትክክለኛ ስምምነት እንዳለ በመግለፅ፤ ቤተሰቡ አስከሬኑን ለዛምቢያ ተወካዮች እንዲያስተላልፍ አዟል።

ቤተሰቡ ይግባኝ በማለቱ አስከሬኑ ወደ ዛምቢያ እንዲመለስ የተሰጠው ትዕዛዝ የይግባኝ ውሳኔ እስኪተላለፍ ድረስ ታግዷል።

በ68 ዓመታቸው ያረፉት ሉንጉ፤ እ.ኤ.አ ከ2015 እስከ 2021 የዛምቢያ ፕሬዝዳንት ነበሩ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0