የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ኤም23 አማፂያን ስምምነት ባልተፈታ ቅድመ ሁኔታ ምክንያት ከቁልፍ የጊዜ ገደብ ዋዜማ መስተጓጐል እንደገጠመው ተሠማ

የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ኤም23 አማፂያን ስምምነት ባልተፈታ ቅድመ ሁኔታ ምክንያት ከቁልፍ የጊዜ ገደብ ዋዜማ መስተጓጐል እንደገጠመው ተሠማ
ሁለቱ ወገኖች በትናትናው ዕለት በዶሃ ይገናኛሉ ተብሎ ቢጠበቅም፤ ኳታር የግብዣ ጥሪ ሳትልክ መቅረቷን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮቹን በመጥቀስ የኮንጎ ሚዲያ ዘግቧል።
የቆመው የሰላም ሂደት፦
▪ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ኤም23 ሐምሌ 12 በዶሃ ቅድመ የሰላም ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን እስከ ሐምሌ 22 ድረስ የመጀመሪያ እርምጃ ለመውሰድ የጊዜ ሰሌዳ ተቀምጦላቸው ነበር።
▪ ዕቅዱ እስከ ነሐሴ 2 መደበኛ ንግግር ለመጀመር እና ነሐሴ 12 ድረስ የመጨረሻ የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ ያስቀመጠ ነበር።
▪ ሆኖም ኤም23 ከንግግሩ በፊት ከ700 በላይ አማፂያን እስረኞች መፈታት እንዳለባቸው አስረግጧል።
▪ ኪንሻሳ ድርድሩ ከተጀመረ በኋላ ጉዳያቸው በግል ይታያል በማለት ከድርድሩ በፊት ለመልቀቅ አሻፈረኝ ብላለች።
▪ የኳታር አደራዳሪዎች፤ ንግግሩን በድጋሚ ለማስጀመር፣ አቋሞችን ለማስታረቅ እና የእስረኞችን መፈታት ለማመቻቸት እየሠሩ እንደሆነ በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች
ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ኮንጎ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቱ እንደገና ማገርሸቱ ተዘግቧል። የተመድ የሰብዓዊ መብት ኃላፊ የኤም23 አማፂያንን ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በተቃራኒ ከ310 በላይ ንጹሃን ዜጎችን ገድለዋል በማለት ሲከሱ ቡድኑ ግን አስተባብሏል።
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X