“ፑቲን የሚፈልጉት መደራደር ነው” - የቤላሩስ ፕሬዝዳንት

ሰብስክራይብ

“ፑቲን የሚፈልጉት መደራደር ነው” - የቤላሩስ ፕሬዝዳንት

አሌክሳንደር ሉካሼንኮ የዩክሬን ቀውስን በተመለከተ ለታይም መጽሔት ቀጥተኛ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ድርድሮች በጥበብ ከታካሄዱ እና ሩሲያ እና ዩክሬን አንዳቸው ለሌላኛቸው ሰጥቶ መቀበልን ከፈቀዱ የጋራ መግባባት ላይ ይደረሳል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ያኔ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ፈጽሞ አትዋጋም ብለዋል፡፡

ስለፑቲን ፍላጎት በተጠየቁ ጊዜም  “በመጀመሪያ ፑቲን የሚፈልጉት መደራደር ነው፡፡ አሜሪካውያኑ አራቱን ክልሎች በሕጋዊ መንገድ በሩሲያ ግዛትነት እውቅና ከሰጡ ለሩሲያ በቂ ይመስለኛል” ሲሉ መልሰዋል፡፡    

“ፑቲንም ሆነ የሩሲያ ወታደራዊ-ፖለቲካዊ አመራሮች ከኔቶ ጋር የመዋጋት ዓላማ የላቸውም” በማለት አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡ 

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0