የአሜሪካ፣ የቻይና፣ የብራዚል እና የደቡብ አፍሪካ መሪዎች በ47ኛው የደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገራት ማኅበር ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ - ማሌዥያ

ሰብስክራይብ

የአሜሪካ፣ የቻይና፣ የብራዚል እና የደቡብ አፍሪካ መሪዎች በ47ኛው የደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገራት ማኅበር ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ - ማሌዥያ

የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም 58ኛውን የደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀራት ማኅበር ቀን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር “መታደማቸውን ማረጋገጥ ብቻ ቀዳሚው እርምጃ ነው፡፡ ማሌዥያን እና ስብሰባውን ጨርሰው ሲወጡ ጊዜያቸው በጥሩ እንዳለፈ እንዲሰማቸው ማረጋገጥ ትልቁ የቤት ሥራቸን ነው፡፡ ጉብኝታቸው ዘላቂ ዋጋ ማስገኘቱን ማረጋገጥ አለብን፡፡ የዓለም ዐይኖች በእኛ ላይ ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ ለሁነቱ ስኬት መትጋት አለብን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጉባኤው 10 የደቡብ ምሥራቅ እስያ ሀገራት ማኅበር አባል ሀገራትን እና የማኅበሩን የምክክር አጋሮች በማሰባሰብ የቀጣናዊ ደህንነት፣ የኢኮኖሚ ትብብር እና አሳሳቢ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፡፡

ከማኅበሩ የምክክር አጋሮች መካከል ቻይና፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ሕንድ፣ አውስትራሊያ፣ ኒው ዚላንድ፣ ካናዳ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ የአውሮፓ ሕብረት እና እንግሊዝ ይገኙበታል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሙሉ ንግግር ይመልከቱ!

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0