ደቡብ አፍሪካ በቤተ-ሙከራ የሚመረቱ አልማዞች መስፋፋትን ተከትሎ የተፈጥሮ አልማዝ ምርቶችን ለማበረታታት ወስናለች
19:14 08.08.2025 (የተሻሻለ: 19:24 08.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱደቡብ አፍሪካ በቤተ-ሙከራ የሚመረቱ አልማዞች መስፋፋትን ተከትሎ የተፈጥሮ አልማዝ ምርቶችን ለማበረታታት ወስናለች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ በቤተ-ሙከራ የሚመረቱ አልማዞች መስፋፋትን ተከትሎ የተፈጥሮ አልማዝ ምርቶችን ለማበረታታት ወስናለች
የሀገሪቱ ካቢኔ የደቡብ አፍሪካ የኢኮኖሚ እድገትን እና የሥራ እድልን መደገፍ ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም የተፈጥሮ አልማዝ ኢንዱስትሪን ለማሳደግ በዓለም አቀፍ ስምምነቶች ላይ ለመሳተፍ መወሰኑን መንግሥት በመግለጫው አስታውቋል።
ለዚህ ዓላማ ሲባልም አልማዝ አምራች ኩባንያዎች ከዓመታዊው ያልተጣራ የአልማዝ ሽያጭ ገቢ 1 በመቶ እንዲከፍሉ እንደሚገደዱ መግለጫው ገልጿል፡፡
ከዓለም ስድስተኛዋ የዳይመንድ አምራች ደቡብ አፍሪካ፤ በ2024 ምርቷ በ9.36 በመቶ መቀነሱን የኪምበርሊ ፕሮሰስ ዓመታዊ መረጃ ያሳያል፡፡
የማዕድን ሀብት ሚኒስትር ግዌዴ ማንታሼ፤ “በቤተ-ሙከራ የሚመረቱ አልማዞች ድርሻችንን እየወሰዱብን ነው፡፡ ችግሩን ለመቀልበስ የተፈጥሮ አልማዞችን የማስተዋወቅ ጣልቃ ገብነት አስፈላጊ መሆኑን አምናለሁ” ሲሉ በዚህ ሳምንት ከአልማዝ ኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X