🈸 የምዕራባውያንን ተፅዕኖ ለመመከት የበለፀገው የልጆች መተግበሪያ

ሰብስክራይብ

🈸 የምዕራባውያንን ተፅዕኖ ለመመከት የበለፀገው የልጆች መተግበሪያ

ህጻናት እና ታዳጊዎችን ከምዕራባውያን የባሕል ተጽዕኖ ለመጠበቅ፤ ሀገር በቀል የሥነ ምግባር እሳቤዎችን እና ዕውቀቶችን በዲጂታል መሣሪያዎች በስፋት ማቅረብ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ልጆች ሱፐር አፕ አበልጻጊዎች ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አቶ አቤል ሰሙ፤ ምዕራባዊያን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ስልተ ኑሯቸውን በአፍሪካ ሀገራት ላይ መጫናቸውን አንስተው፤ መተግበሪያውም ልጆች የራሳቸውን ነገር እንዲያውቁ እና እንዲወዱ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

አቶ ፍቃዱ አበራ በበኩላቸው፤ "መተግበሪያው ህጻናት እና ታዳጊዎች ባሕል፣ ወግ እና ሥርዓታቸውን እንዲያውቁ እንዲሁም የንባብ እና የቋንቋ ክህሎታቸውን እንዲያጎለብቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ ክፍሎች አሉት" ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0