‍ ባለፉት አስርት ዓመታት የእናቶችን ሞት መቀነስ ቢቻልም አሁንም ብዙ ሥራዎች እንደሚቀሩ የሕክምና ባለሙያዎቹ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ባለፉት አስርት ዓመታት የእናቶችን ሞት መቀነስ ቢቻልም አሁንም ብዙ ሥራዎች እንደሚቀሩ የሕክምና ባለሙያዎቹ ተናገሩ

ለእናቶች ሞት መንስኤ የሚሆኑ የጤና ችግሮችን ለመፍታት ለቅድመ ወሊድ ምርመራ እና ለሕክምና ጣልቃ ገብነት ልዩ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ የወሊድ እና የማሕጸን ሐኪሞቹ ዶ/ር ታጠቅ ተስፋዬ እና ዶ/ር ምስክር አንበርብር ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ምስክር አንበርብር፤ በእርግዝና ወቅት እና ከወሊድ በኋላ የሚፈጠር ከፍተኛ የደም መፍሰስን ጨምሮ ለእናቶች ሞት መንስኤ የሚሆኑ 80 በመቶ የሚሆኑ የጤና ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል ይላሉ፡፡

ደ/ር ታጠቅ ተስፋዬ በበኩላቸው፤ ባለፉት አስርት ዓመታት ከ100 ሺህ ወሊድ ያጋጥም የነበረውን 871 የእናቶች ሞት ወደ 195 ማውረድ ቢቻልም አሁንም የተለያዩ አካላትን ቅንጅት የሚፈልጉ መጠነ ሰፊ ሥራዎች መኖራቸውን አንስተዋል።

የሙያ አጋራቸው ዶ/ር ምስክርም "የእናቶች ሞትን በመቀነስ ረገድ አበረታች ሥራዎች ተሠርተዋል። ሆኖም በዘላቂ የልማት ግቦች ከተያዘው ውጥን አንፃር ረጅም መንገድ ከፊታችን ይቀረናል" ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0