አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሩሲያ ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናከረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሩሲያ ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናከረ
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሩሲያ ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናከረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.08.2025
ሰብስክራይብ

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሩሲያ ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናከረ

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በብሪክስ ማዕቀፍ ምርምር እና ትምህርትን ለማሳደግ ያለመ ሳይንሳዊ ትብብር ከሩሲያው ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር ጀምሯል፡፡

በአዳማ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አበበ በላይ፤ ትብብሩ እያደገ ላለው የኢትዮጵያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን ጥቅም በመጥቀስ፤ "መሰል ትብብር በተለይ እንደ ካንሰር ምርመራ እና የመድኃኒት አቅርቦት ባሉ መስኮች በጣም ጠቃሚ መሆኑን” ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ተመራማሪው የትብብር ስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦችን ጠቅሰዋል፦

ሳይንሳዊ መሣሪያዎች መጋራት፣

ሳይንሳዊ ጉባኤዎች፣ ወርክሾፖች እና ሥልጠናዎችን ማዘጋጀት፣

የመምህራን፣ የተመራማሪዎች እና የተማሪዎች የጋራ ልውውጥ ናቸው፡፡

ወደ ሩሲያ በማቅናት ሴቫስቶፖል ስቴት ዩኒቨርሲቲ በናኖቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረውን የምርምር ጉብኝት የሚያደርጉት የፊዚክስ ፕሮፌሰሩ፤ "ናኖ-ተኮር ሥርዓቶችን በመጠቀም መድኃኒቶችን በማምረት ረገድ ጠቃሚ ልምድ አገኛለሁ ብዬ እጠብቃለሁ" ብለዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0