እየተጠበቀ ያለው የአርሜኒያ እና የአዘርባጃን የሰላም ስምምነት ‘ለአርሜኒያ እጅ የመስጠት እርምጃ ነው’ - ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱእየተጠበቀ ያለው የአርሜኒያ እና የአዘርባጃን የሰላም ስምምነት ‘ለአርሜኒያ እጅ የመስጠት እርምጃ ነው’ - ተንታኝ
እየተጠበቀ ያለው የአርሜኒያ እና የአዘርባጃን የሰላም ስምምነት ‘ለአርሜኒያ እጅ የመስጠት እርምጃ ነው’ - ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.08.2025
ሰብስክራይብ

እየተጠበቀ ያለው የአርሜኒያ እና የአዘርባጃን የሰላም ስምምነት ‘ለአርሜኒያ እጅ የመስጠት እርምጃ ነው’ - ተንታኝ

“ይህ የሰላም ስምምነት አይደለም፤ የአርሜኒያ ፍላጎቶች ውሉ ላይ አልተንፀባረቁም” ሲሉ አርሜኒያዊው የቀጣናዊ ደህንነት ተንታኝ ግራንት ሜሊክ ሻኽናዛሪያን ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡

የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓሺንያን እና የአዘርባጃኑ ፕሬዝዳንት አሊዬቭ፤ ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ “ታሪካዊ የሰላም ጉባኤ” ብለው ባወደሱት ስብሰባ ለመገኘት ዛሬ አርብ ዋሽንግተን ላይ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

ተንታኙ ሲቀጥሉ፤ “አዘርባጃን የሕገ-መንግሥት ማሻሻያን ጨምሮ ከአርሜኒያ ብዙ ጠይቃለች፡፡ ፓሺንያን ይህን ታሪካዊ ስምምነት ብለው ይመጻደቁበት ይሆናል፤ ነግር ግን ይህን ሁሉ የሚያደረጉት አርሜናውያንን በውሸት ለማሳመን ነው” ይላሉ፡፡

አርሜኒያ ግዛቷ ውስጥ የሚገኘውን ብቸኛ መተላለፊያ አሜሪካ ለብቻዋ እንድትጠቀም ማቀዷንም በተመለከተ አንድምታውን ጠቁመዋል፦

▪ ሉዓላዊነትን ማጣት፣

▪ የግጭቶች መስፋፋት ስጋት፣

▪ ቀጣናዊ ሚዛን ማዛባት፣

▪ ከሩሲያ እና ከሌሎች አጋሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ማዳከም፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0