በሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ከኩታ ገጥም እርሻ ምርት ባሻገር ወደ ማቀነባበር እና ዕሴት ወደ መጨመር ሽግግር ይደረጋል - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ከኩታ ገጥም እርሻ ምርት ባሻገር ወደ ማቀነባበር እና ዕሴት ወደ መጨመር ሽግግር ይደረጋል - ባለሙያ
በሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ከኩታ ገጥም እርሻ ምርት ባሻገር ወደ ማቀነባበር እና ዕሴት ወደ መጨመር ሽግግር ይደረጋል - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.08.2025
ሰብስክራይብ

በሁለተኛው ምዕራፍ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ከኩታ ገጥም እርሻ ምርት ባሻገር ወደ ማቀነባበር እና ዕሴት ወደ መጨመር ሽግግር ይደረጋል - ባለሙያ

አርሶ አደሮችን ሕጋዊ በማድረግ በኩታ ገጠም (ክላስተር) የሚገኘውን ምርት ለግብርና ማቀነባበሪያ ማቅረብ እና ዕሴት ለመጨመር የሚሆኑ አማራጮች ማየት እንደሚገባ ከፍተኛ የግብርና ተመራማሪ ዳኛቸው ሉሌ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡

“ስለዚህ የተመረተው ምርት እዚያው ተቀነባብሮ እሴት ተጨምሮብት ቢሄድ የተሻለ ዋጋ ያገኛል፡፡ ለአርሶ አደሩም ለተጠቃሚውም ደግሞ እጅግ በጣም ቆንጆ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ከ300 ወረዳዎች ውስጥ 50 ወረዳ መርጠን ወደ ኩባንያ ደረጃ እናደርሳቸዋለን የምንለው በእሴት ሰንሰለት ነው” ብለዋል፡፡

ከፍተኛ የግብርና ተመራማሪው በይርጋለም እና በሞጆ አካባቢ የአቮካዶ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በግለሰቦች መከፈታቸውን ለአብነት በመጥቀስ፤ ሌሎች ምርቶችም በዚያ መልኩ እንደሚቀጥሉ ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡

ዳኛቸው “ከዚህ በኋዋላ ወደ አግሮ ኢንዱስትሪ የሚሄዱ ወደ አግሮ ኢንዱስትሪ፤ ወደ ኤክስፖርት የሚሄዱ ወደ ኤክስፖርት፣ በራሳቸው የሚሠሯቸውን ሥራዎች ሠርተው፤ ልጆቻቸው እዚያው ሥራ አግኝተው የገጠር ሽግግር እውን እንድናደርግ የሚያስችል መንገድ የሚከፍቱ፣ ዲጂታል ግብርና ያላቸው፣ ሜካናይዜሽን ያላቸው፣ ግብዓት ያላቸው ኩባንያዎችን እውን ለማድረግ ነው አሁን እየሠራን ያለነው” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0