አዋሽ ወንዝ ሞልቶ 9 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸ ሲዘገብ፤ በመጪዎቹ ወራት ደግሞ ከመደበኛ በላይ የዝናብ ይኖራል ተብሏል

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአዋሽ ወንዝ ሞልቶ 9 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸ ሲዘገብ፤ በመጪዎቹ ወራት ደግሞ ከመደበኛ በላይ የዝናብ ይኖራል ተብሏል
አዋሽ ወንዝ ሞልቶ 9 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸ ሲዘገብ፤ በመጪዎቹ ወራት ደግሞ ከመደበኛ በላይ የዝናብ ይኖራል ተብሏል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.08.2025
ሰብስክራይብ

አዋሽ ወንዝ ሞልቶ 9 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸ ሲዘገብ፤ በመጪዎቹ ወራት ደግሞ ከመደበኛ በላይ የዝናብ ይኖራል ተብሏል

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኮምንኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኤቢሴ ተርፋ የነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም መረጃን ሳይጨምር ከወንዙ መሙላት ጋር በተያያዘ የተፈናቀሉ ከ9 ሺህ በላይ ሰዎች በሁለት ወረዳዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

የውሃ ሙላቱ ከነዋሪዎች መፈናቀል ባለፈ የንብረት፣ የቤት እንስሳዎች በውሃ መወሰድ እና የበርካታ ሄክታር ሰብል ውድመት አስከትሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በነሐሴ እና መስከረም ወራት ላይ ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስጠንቅቋል፡፡

ኢኒስቲትዩቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ሰብል ላይ የውሃ መተኛት፣ የመሬት መንሸራተት እና የከባድ ዝናብ ቅጽበታዊ ጎርፍ ማስከተል ስለሚኖር ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0