የኢትዮጵያ የኢነተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 55 ሚሊየን እንደደረሠ ተገለጸ
13:12 08.08.2025 (የተሻሻለ: 13:14 08.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የኢነተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 55 ሚሊየን እንደደረሠ ተገለጸ
ቁጥሩ የኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ ከመጀመሩ በፊት 17 ሚሊየን እንደነበር የኢኖቬሽና እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ አቢዮት ባዩ ገልፀዋል፡፡
25 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ለፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ እንደተመዘገቡም አክለዋል፡፡ በ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ 1.8 ሚሊየን ዜጎች እየተሳተፉ እንደሆነ እና 1 ሚሊየን የሚሆኑት የእውቅና ሠርትፍኬት እንደተሠጣቸውም ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በ2018 ዓ.ም ህዳር ወር ፊውቸር ቴክ ኤክስፖ 2025ን ታስተናግዳለች፡፡ ዝግጅቱ ስታርታፕችን ከኢንቨስተሮች ለማገናኘት እና የንግድ አጋርነቶችን ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተነግሯል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X