በተባበሩት መንግሥታት የኢራን መልዕክተኛ የፈረንሳይን “መሠረት የለሽ” የኒውክሌር ውንጀላዎች አወገዙ
10:51 08.08.2025 (የተሻሻለ: 10:54 08.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበተባበሩት መንግሥታት የኢራን መልዕክተኛ የፈረንሳይን “መሠረት የለሽ” የኒውክሌር ውንጀላዎች አወገዙ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በተባበሩት መንግሥታት የኢራን መልዕክተኛ የፈረንሳይን “መሠረት የለሽ” የኒውክሌር ውንጀላዎች አወገዙ
በመንግሥታቱ የኢራን መልዕክተኛ ሰኢድ ኢራቫኒ፤ የፈረንሳይ አምባሳደር ኢራን “የኒውክሌር ጦር በማመረት ቀውስ” አስነስታለች በማለት መክሰሳቸውን ተክትሎ በሰጡት ምላሽ፤ በ ”ግብዝነት” እና “እውነታዎችን ሆነ ብሎ በማሳከር” ፈረንሳይን ኮንነዋል፡፡
መልዕክተኛው ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ እና ለፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በጻፉት ደብዳቤ፤ “መሠረተ የለሽ” የሆኑትን ንግግሮች ውድቅ በማድረግ፤ ፈረንሳይ የኒውክሌር መሣሪያ አለማስፋፋት ስምምነት ግዴታዋን መወጣት ባለመቻል እና የእስራኤልን ስውር የኒውክሌር መርሃ-ግብር በመርዳት ከስሰዋል፡፡
ፈረንሳይ በዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥበቃ በሚደረግላቸው የኢራን የኒውክሌር መሠረተ ልማቶች ላይ እስራኤል ሰኔ 13 ቀን 2025 የፈጸመችውን ጥቃት አለማውገዟን ጠቁመዋል፡፡ ድርጊቱም ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጥስና የኒውክሌር ጦር መሣሪያ አለማስፋፋትን የሚያዳክም ነው ብለዋል፡፡
“የኢራን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ሰላማዊ እና ሙሉ በሙሉ ግልጽ ነው፡፡ ኢራን በዓለም አቀፉ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ አለማስፋፋት ስምምነት ስር ያሉ ግዴታዎቿን ማክበሯን ቀጥላለች” ሲሉ ጽፈዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X