የደቡባዊው ዓለም የመልስ ምት፦ የአሜሪካ ቀረጥ ዛቻዎች ብሪክስን ወደ ሙሉ የኢኮኖሚ ጥምረትነት እየቀየሩት ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየደቡባዊው ዓለም የመልስ ምት፦ የአሜሪካ ቀረጥ ዛቻዎች ብሪክስን ወደ ሙሉ የኢኮኖሚ ጥምረትነት እየቀየሩት ነው
የደቡባዊው ዓለም የመልስ ምት፦ የአሜሪካ ቀረጥ ዛቻዎች ብሪክስን ወደ ሙሉ የኢኮኖሚ ጥምረትነት እየቀየሩት ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.08.2025
ሰብስክራይብ

የደቡባዊው ዓለም የመልስ ምት፦ የአሜሪካ ቀረጥ ዛቻዎች ብሪክስን ወደ ሙሉ የኢኮኖሚ ጥምረትነት እየቀየሩት ነው

በሆንግ ኮንግ መቀመጫቸውን ያደረገት የፖለቲካ እና እና የፋይናንስ ባለሙያ አንጄሎ ጁሊያኖ፤ “የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ፤ የአሜሪካ የቅርብ ጊዜ ቀረጦችን ለመቀልበስ ብሪክስ የጋራ ምላሽ እንዲሰጥ ያደረጉት ይፋዊ ጥሪ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣው የጥምረቱን ሕብረት እና ፖለቲካዊ አይደፈሬነት ያጎላል” ሲሉ ለስፑትኒክ ተናገረዋል፡፡

ብሪክስ ምን አይነት ያጸፋ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ገና ባይታወቅም፤ ጁሊያኖ የሚከተሉትን ያካተተ እርምጃዎች ሊወስዱ እንደሚችሉ አስቀምጠዋል፦

በየመገበያያ ገንዘባቸው የሚያደርጉትን ንግድ ማፋፋም፣

የአዲስ ልማት ባንክን የማንቀሳቀስ አቅም እና የብድር ኃይሉን ማጠናከር፣

አማራጭ የስዊፍት (የባንክ ለባንክ የፋይናንስ ቴሌኮሙኒኬሽን) ማልማት እና ማሳደግ፣

በዓለም ንግድ ድርጅት በኩል “በአሜሪካ ቀረጦች ላይ የተቀናጀ ተግዳሮትን መደገፍ”፡፡

“እነዚህ እርምጃዎች ሲደመሩ የአሜሪካ ዶላር ዓለም አቀፍ የበላይነትን በተጨባጭ ይቀንሳሉ፡፡ ይህም ዋሽንግተንን በኢኮኖሚ በማዳከም እና ከፋይናንስ ቅድምናዋ የመጣውን የጂኦፖለቲካዊ ልዩ እድሏን የሚሸረሽር ነው” ሲሉ ጂሊያኖ አክለዋል፡፡

የብሪክስ ጥምረት በአንድ ጀምበር ወደዚህ ደረጃ አልመጣም ያሉት ተንታኙ፤ ዓመታትን በተቋማዊ ግንባታ ማሳለፉ እና በቅርቡ ማስፋፊያው የበለጠ ያበበው የአባል ሀገራቱን የጋራ ኢኮኖሚ ሲያሳድግ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

የቅርብ ጊዜ ቀረጦችን ለማዕቀብ የመጠቀም የአሜሪካ ጠብ አጫሪነት “በጥምረቱ ውስጥ አንድነትን አቀጣጥሏል፡፡”

ለዓመታት “ብሪክስን በጣም አሳንሰው የተመለከቱ” እና “ከመሠረቱ የተበታተነ እና ትርጉም ያለው የጋራ እርምጃ የመውሰድ አቅም የሌለው” አድርገው ሲዘባበቱበት የቆዩ የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች፤ ከዚህ በኋላ እንደዛ እንዳለሆነ ከስህተታቸው ተምረዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0