የትራምፕ አዲስ የፀረ-ሩሲያ ማዕቀብ ዛቻዎች ሞስኮን ዒላማ ያደረጉ አይደሉም - ባለሙያ
20:45 07.08.2025 (የተሻሻለ: 20:54 07.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የትራምፕ አዲስ የፀረ-ሩሲያ ማዕቀብ ዛቻዎች ሞስኮን ዒላማ ያደረጉ አይደሉም - ባለሙያ
በሩሲያ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቦባከር መሐመድ አባካር ሁሴን ሞስኮ በነባር ማዕቀቦች ስር ከመሆኗ አኳያ ለማናቸውም አዲስ እቀባዎች "አትንበርከክም" ሲሉ ለስፑትኒክ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
ባለሙያው እንደሚሉት የትራምፕ "የማባበያ እና የማስፈራሪያ" አካሄድ እንዲሁም "በማዕቀብ የማስፈራራት ቋንቋ" በዋናነት "አውሮፓውያንን ለማረጋጋት" የታለመ እንጂ ሩሲያን የሚቀይር አይደለም፡፡
"ለነሱ (ለአውሮፓውያን) በአሜሪካ ኢኮኖሚ ውስጥ ፈሰስ የሚያደርጉት ገንዘብ እንደማይባክን እንዲገባቸው ብቻ ለማድረግ ነው" ብለዋል።
የፑቲን እና የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ዊትኮፍ ስብሰባን ተከትሎ፤ ትራምፕ ከ24 እስከ 36 ሠዓታት ውስጥ በሩሲያ ላይ ሊጣሉ የሚችሉ አዳዲስ ማዕቀቦችን በተመለከተ ይወስናሉ ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X