ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ጠየቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ጠየቀች
ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ጠየቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.08.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ጠየቀች

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ሥሜ፤ የቱርክሜንስታኑ ጉባኤ ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥ እና ዓለም ለጉዳዩ ያለው ቁርጠኝነት ዳግም ይታደስበታል ብላ እንደምትጠብቅ ተናግረዋል፡፡

“የባሕር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ቀጥተኛ የባሕር በር መተላለፊያ ባለማግኘታቸው፣ ከፍተኛ የትራስፖርት ወጪ እና መሠረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ አለመሟላትን ጨምሮ በሌሎች መሠረታዊ ችግሮች እየተፈተኑ እንደሚገኙ” በሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት የባሕር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሩ በንግግራቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ይገኙበታል፦

◻ የባሕር በር መሠረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ሙሉ ለሙሉ ሊተገበሩ ይገባል፡፡

◻ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት እኩል የማሪታይም መብታቸው መረጋገጥ አለበት፡፡

◻ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ያልተቋረጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባሕር መተላለፊያ የማግኘት መብታቸው ሊከበር ይገባል፡፡

◻ የባሕር በር የማግኘት መብት ላይ የሚሠሩ ተቋማት ሀገራትን በእኩልነት ማስተናገድ አለባቸው፡፡

ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር የማግኘት መብታቸውን እውን ማድረግ በሚቻልባቸው አማራጮች ላይ ሙያዊ ምክረ ሀሳቦችን የሚያቀርብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን መቋቋሙን እንደምታደንቅም ገልፀዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ጠየቀች
ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ጠየቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.08.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0