ኢትዮጵያ ከአየር ትራንስፖርት የአገልግሎት ክፍያ 3.3 ቢሊየን ብር በላይ አገኘች
19:31 07.08.2025 (የተሻሻለ: 19:34 07.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከአየር ትራንስፖርት የአገልግሎት ክፍያ 3.3 ቢሊየን ብር በላይ አገኘች
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን፤ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያን አየር ክልል አቋርጠው ሲገቡ በሚከፍሉት የ “ኤር ናቪጌሽን” ክፍያ ነው ገቢውን ያገኘው፡፡
በታሪክ ከ300 ሚሊየን ብር በልጦ አያውቅም የተባለው የዘርፉ ገቢ፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል።
በ2016 በጀት ዓመት 2 ቢሊየን ብር የነበረው ገቢ፤ በ2017 ደግሞ ከ3 ቢሊየን በላይ ሆኖ መመዝገቡን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X