የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለቀጣናው የኃይል ትስስር ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለቀጣናው የኃይል ትስስር ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል

ብሪክስ ተደማጭነታቸው እያደገ ካሉ ጥምረቶች አንዱ መሆኑን ያወሱት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ፤ እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ሩሲያ ያሉት አባል ሀገራቱም የኢትዮጵያ ጠንካራ አጋሮች መሆናቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃልምልልስ አስታውሰዋል፡፡

"ጥምረቱ መሠረተ ልማታችንን ለማስፋት እንዲሁም በኃይል ትስስር ክልላዊ ውህደትን ለማረጋገጥ እንደ ተቋም ተጨማሪ አቅም ይፈጥርልናል። ጥምረቱ ለተቋሙ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት" ብለዋል።

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይልን በርካሽ በቀጣናው በማቅረብ ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ የድርሻዋን እየተወጣች መሆኗንም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0