ስፑትኒክ አፍሪካ በተለየ አካሄድ ለሌሎች አርዓያ እንዲሆን ይጠበቅበታል

ሰብስክራይብ

ስፑትኒክ አፍሪካ በተለየ አካሄድ ለሌሎች አርዓያ እንዲሆን ይጠበቅበታል

ስፑትኒክ አፍሪካ ፍትሕን፣ አካታችነትን እና የሙያ ሥነ-ምግባርን መሠረት አድርጎ በመሥራት ለሌሎች ሚዲያዎች አርዓያ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት የገለጹት፤ የደቡብ ትብብር ድርጅት የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ዲጂታላይዜሽን ማሻሻያ ዋና ጸሃፊ ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ናቸው።

ዋና ጸሃፊው ስፑትኒክ አፍሪካ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከተጠለፉበት ራስን የማግነን አካሄድ በተቃራኒ መሬት ላይ ላሉ እውነታዎች ትኩረት እንደሚሰጥም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

"በሚዲያዎች ሲገነባ የነበረ የውሸት ትርክት ሀገሬን እንዴት ሲጎዳ እንደነበረ በተደጋጋሚ አይቻለሁ። በዚህ ረገድ ሚዲያው ከዚህ ቀደም ከነበረው አካሄድ የተለየ ነገር እንደሚያሳየን እጠብቃለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0