በቢሾፍቱ የጣለው ከፍተኛ ንፋስና በረዶ በተቋማት እና በእርሻዎች ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ
16:10 07.08.2025 (የተሻሻለ: 16:14 07.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በቢሾፍቱ የጣለው ከፍተኛ ንፋስና በረዶ በተቋማት እና በእርሻዎች ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ
በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በምተገኘው ከተማ የጣለው ዝናብ፤ በአካባቢው በሚገኙ የምርምር ተቋማት፣ የአበባ እና የፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡
“በቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል በተለይም በእንስሳት እና ሰብል ምርምር ፕሮግራሞች ላይ መጠነ-ሰፊ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ሙከራ የሚደረግባቸውን የምርምር ሥራዎችን ጭምር አበላሽቷል፤ ሕንጻዎችም አፈራርሷል፤ ትልልቅ ዛፎችን ወደ ምርምር እና የቢሮ ሕንጻዎች ላይ በመገንደስ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል” ሲል የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩትም በንብረት ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ይፋ አድርጓል፡፡
ከትናንት በስቲያ ሁለት ዋና ዋና እርሻዎች ላይ የሚገኙ ግሪን ሐውሶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸዉን እና ሌሎች ስምንት የሚሆኑ እርሻዎችም ከፍተኛ የሚባል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በደረሰው አደጋ ምክንያት በአካባቢው የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ይህ ደግሞ የእርሻ ሥራዎችን ይበልጥ ተፅዕኖ ዉስጥ እንደሚጥል ተገልጿል፡፡
በእርሻ ማሳዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት መጠን ለማወቅ ዝርዝር ጉዳዮች እየተጣሩ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ