የ2017 ኢትዮጵያ የተቀናጀ ሀገር አቀፍ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ለ18.5 ሚሊየን ሕጻናት እንደተዳረሰ ተገለፀ
13:29 07.08.2025 (የተሻሻለ: 13:34 07.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የ2017 ኢትዮጵያ የተቀናጀ ሀገር አቀፍ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ለ18.5 ሚሊየን ሕጻናት እንደተዳረሰ ተገለፀ
ኢትዮጵያ የ2025 ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ዘመቻ የታለመውን ግብ 99 በመቶ አሳክቶ መጠናቀቁን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ቀናት የቆየው ዘመቻ በ12 ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች፤ ከ9 እስከ 59 ወር የሆኑ ሕጻናት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ነበር።
የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ኦውል ካሉዋ፤ የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ የሕጻናት ሞትን ለመቀነስ የክትባት አሰጣጥን እና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ሥርዓቶችን ለማጠናከር የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X