ፑቲን እና ትራምፕ ሊገናኙ ነው
ሁለቱ መሪዎች በሚገናኙበት ቦታ ዙሪያ ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይፋ እንደሚሆን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት ዩሪ አሻኮቭ ተናግረዋል።
ሁለቱ አካላት በጉዳዩ ላይ ዝግጅት መጀመራቸውን ረዳቱ አክለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ዊትኮፍ በፑቲን፣ ትራምፕ እና ዘለንስኪ መካከል የሶስትዮሽ ውይይት ሃሳብን ቢያነሱም ሞስኮ ግን ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠችበትም ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ረዳት ተናግረዋል።
የሚቀጥለው ሳምንት እንዲካሄድ የተወሰነው የፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ ዝግጅት ምን ያህል ቀናት እንደሚወስድ ለመናገር አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X