የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኤሌክትሪክ ሽያጭ 75.4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
10:55 07.08.2025 (የተሻሻለ: 11:04 07.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኤሌክትሪክ ሽያጭ 75.4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
በበጀት ዓመቱ 25.18 ቴራ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ተሸጧል ያሉት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ፤ ከዚህም ውስጥ 93 በመቶ ለሀገር ውስጥ እንዲሁም 7 በመቶ ለውጭ ሀገራት ለሽያጭ እንደቀረበ ገልፀዋል።
እንደ ኃላፊው ማብራሪያ፦
60 በመቶ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣
27 በመቶ ለዳታ ማይኒንግ፣
6 በመቶ ለኢንዱስትሪዎች፣
5 በመቶ ለኬንያ፣
2 በመቶው ደግሞ ለጅቡቲ ተሽጧል ።
ከአጠቃላይ ሽያጩ 74.05 ቢሊየን ብር ከኃይል ሽያጭ፤ 1.41 ቢሊየን ብር ከተጓዳኝ አገልግሎቶች መገኘቱንም የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም በማስመልከት ባቀረቡት ሪፖርት ይፋ አድርገዋል።
እንደ ኢንጂነር አሸብር ገለጻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከውኃ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይልን በማመንጨት ከአፍሪካ ቀዳሚ ነው።
ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በበጀት ዓመቱ 7 ሺ 910 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ላይ ደርሷል። ግድቡ ሲጠናቀቅ ወደ 9ሺ ሜጋ ዋት እንደሚያድግም ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
