በደቡብ አፍሪካ የውስጥ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ ጣለቃ ገብነት የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት አዳክሞታል - የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
17:16 06.08.2025 (የተሻሻለ: 17:24 06.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበደቡብ አፍሪካ የውስጥ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ ጣለቃ ገብነት የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት አዳክሞታል - የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በደቡብ አፍሪካ የውስጥ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ ጣለቃ ገብነት የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት አዳክሞታል - የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
“በቀደመው ዘመን ልክ እንደ አሁን ሌላ መንግሥት በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ሲፈልግ አላስተዋልንም” ሲሉ ለምዕራባውያን ሚዲያ የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ፤ የወቅቱ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ባለፉት 30 ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን አስምረውበታል፡፡
ግንኙነታቸው እየሻከረ የሄደው በሁለት ቁልፍ ሁነቶች ምክንያት ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት እስራኤልን በዘር ማጥፋት ወንጀል መክሰሷ እና የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር የአሜሪካን ፖሊሲዎች መተቸታቸውን ተከተሎ ከዋሽንግተን በመባረራቸው ነው፡፡
የላሞላ መግለጫ በሀገሪቱ 30 ሺህ ሥራ አጦችን ይፈጥራል ተብሎ የተሰጋው የአሜሪካ የቀረጥ ማስፈራሪያን ጨምሮ በብዙ ጉዳዮች ላይ ውጥረቶች እየጨመሩ መምጣታቸውን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡
ደቡብ አፍሪካ የንግድ ስምምነት ለመደራደር እና ሉዓላዊነቷን ለማስከበር በነጻ ሀገራት መካከል የጋራ መከባበር አስፈላጊነትን ለማጉላት ተጨባጨ ጥረቶቿን እንደወሰደች ትገልፃለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X