በአክራ እየተደረገ ያለው የአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት ጉባኤ ዓለም አቀፍ የጤና አስተዳደር እንዲሻሻል ጠየቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአክራ እየተደረገ ያለው የአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት ጉባኤ ዓለም አቀፍ የጤና አስተዳደር እንዲሻሻል ጠየቀ
በአክራ እየተደረገ ያለው የአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት ጉባኤ ዓለም አቀፍ የጤና አስተዳደር እንዲሻሻል ጠየቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.08.2025
ሰብስክራይብ

በአክራ እየተደረገ ያለው የአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት ጉባኤ ዓለም አቀፍ የጤና አስተዳደር እንዲሻሻል ጠየቀ

በጋናው ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሐማ የተመራው የማክሰኞው ጉባኤ፤ በብሔራዊ አመራር፣ በባለቤትነት እና በኢንቨስትመንት የጤና ሉዓላዊነትን ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

ማሐማ የአፍሪካን ድምጽ እና ፈጠራን ለረዥም ጊዜ ያገለሉ ዓለም አቀፍ የጤና ሥርዓቶች በአዲስ እንዲዋቀሩ ጠይቀዋል፡፡ ጽኑ፣ ክብርን የሚያስጠብቁ እና ፍትሐዊ የአፍሪካ የጤና ሥርዓትቶች እንዲሁም በአኅጉሪቱ አዲስ የጤና ፋይናንስ አካሄድ እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አፍሪካ መር ጉባኤው የላቀ የጤና አገልግሎት ለሁሉም ለማድረስ፦

🟠 ለአስቸኳይ የጤና ማሻሻያ ግፊት ማድረግ፣

🟠 ብሔራዊ አስተዳደርን እና ፋይናንስን ማጠናከር፣

🟠 ጊዜ ያለፈባቸውን ሥርዓቶች ማዘመንን ጠይቋል፡፡

የጉባኤው ዋና ውጤቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

🟠 የዓለም አቀፍ የጤና አስተዳደረን ዳግም ለመቅረጽ በአፍሪካ መሪዎች የሚመራ ፕሬዝዳንታዊ የከፍተኛ ደረጃ ግብረ ኃይል ምሥረታ፣

🟠 ቋሚ በሽታዎች ክብካቤ ላይ ኢንቨስትመንት ለማሳደግ የጋና የሕክምና ትረስት ፈንድ ማስጀመር፣

🟠 ሀገራት የገንዘብ ምንጮችን እንዲቀርጹ፣ ጉድለቶችን እንዲለዩ እና ዘላቂ የጤና ፋይናንስን እንዲያቅዱ ለመርዳት ሉዓላዊ ሽግግሮች እና ተቋማዊ ትስስሮችን የማስፋፋት ንቅናቄዎችን ይፋ ማድረግ፣

🟠 የዓለም ጤና ድርጅት ለሀገራት የጤና ፋይናንስ አሰባሰብ መሻሻል የቴክኒክ ድጋፍ ለማደረግ ቁርጠኝነቱን ገልጿል።

በአክራ እየተደረገ ያለው የአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት ጉባኤ ዓለም አቀፍ የጤና አስተዳደር እንዲሻሻል ጠየቀ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0