በአዲስ አበባ 2.2 ሚሊየን በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፍ የበጎ ፈቃድ ዘመቻ ተጀመረ
15:44 06.08.2025 (የተሻሻለ: 15:54 06.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ 2.2 ሚሊየን በጎ ፈቃደኞችን የሚያሳትፍ የበጎ ፈቃድ ዘመቻ ተጀመረ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን፤ ከ805 ሺህ በላይ ደጋፍ የሚሹ ዜጎችን የሚያስጠቅም የክረምት የበጎ ፈቃድ አግልግሎት ንቅናቄ ማስጀመሩን አስታውቋል፡፡
በኮሚሽኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ትብብር ዳይሬክተር ዳዊት ሙሉጌታ፤ ዘመቻው አሳትፊ ስትራቴጂን በመከተል 6.5 ሚሊየን ብር የሚገመት የዕውቀት፣ የሀብት እና የጉልበት ሥራ እንዲያበረክቱ ያበረታታል ብለዋል፡፡
በዚህ መሠረት፦
ለ500 ሺህ ግለሰቦች ምግብ ለማቅረብ፣
የ2 ሺህ 500 ቤቶች እድሳት ለማከናወን፣
40 ሺህ ዩኒት ደም ልገሳ (14 ሺህ ተሰብስቧል) ለማሰባሰብ፣
ለ49 ሺህ ሰዎች ነጻ የጤና ምርመራ ለማድረግ አቅዷል፡፡
በ2017 የበጀት ዓመት ኮሚሽኑ ከ16 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ የበጎ ፈቃድ አግልግሎት 1.7 ሚሊየን ዜጎችን ማገዙን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X