🪉 ለህከምና አገልግሎት አየዋለ ያለው ጥንታዊው የበገና መሳሪያ

ሰብስክራይብ

🪉 ለህከምና አገልግሎት አየዋለ ያለው ጥንታዊው የበገና መሳሪያ        

ባለ አስር አውታሩ በገና ቀድሞውንም መንፈስን አዳሽ የጥሞና መሳሪያ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ዮሀንስ ራዕይ በ53 ቦታዎች ላይ ተጠቅሷል የሚባለው የዜማ መሳሪያ፤ አዲስ አበባ በሚገኘው ግሬስ የህሙማን እና የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ታካሚዎችን ለማስታመም እየዋለ ነው፡፡

በማዕከሉ የበገና ድርደራ የታካሚዎችን መስተጋብር በማጠናከር፣ ደስታን በመፍጠር፣ ጥሩ እንቅልፍ እንዲያገኙ እና ከጭንቀት እንዲወጡ በማድረግ ረገድ አስተዋፃኦ እያደረገ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የግሬስ ክሊኒክ መስራች ዶ/ር ናትናኤል ሀይሉ “የበገና ቴራፒ ያመጣው ለውጥ አለ፡፡ ይህንንም ከታካሚዎቻችን ምስክርነት የምናገኘው ነው፡፡ በገናው ሲደረደር እርጋታ፣ ከጭንቀት መገላገል፣ ደስታ ይታይባቸዋል። የታካሚዎቻችን የደም ግፊት ሲቀንስ ተመልክተናል" ሲል ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።

በማዕከሉ ታኪሚ የሆኑት የ60 ዓመቱ አቶ ሰለሞን ዳንኤል ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

"በጣም ጠቅሞኛል እንጂ...እንቅልፍ ለኔ በፊት በጣም አስቸጋሪ ነበር፤ አሁን ግን ጥሩ እተኛለሁ" ብለዋል።

የበገና ህክምናን በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር ጥናቶች እየተደረጉ እንደሆነ ዶ/ር ናትናኤል ሀይሉ ጨምረው ነግረውናል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ🪉 ለህከምና አገልግሎት አየዋለ ያለው ጥንታዊው የበገና መሳሪያ
🪉 ለህከምና አገልግሎት አየዋለ ያለው ጥንታዊው የበገና መሳሪያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.08.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0