ግሎባል ፈንድ በኬንያ የሚመረተውን የኤችአይቪ መድኃኒት ለሞዛምቢክ አቀረበ
20:01 05.08.2025 (የተሻሻለ: 20:04 05.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ግሎባል ፈንድ በኬንያ የሚመረተውን የኤችአይቪ መድኃኒት ለሞዛምቢክ አቀረበ
ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በሀገር በቀል የኤችአይቪ መድኃኒቶች እና ምርመራዎች በጤና ዘርፍ ራሳቸውን የማስተዳደር አቅምን እያሳደጉ ነው ተብሏል፡፡
በመላው ዓለም የኤችአይቪ፣ የሳንባ ነቀርሳ እና የወባ በሽታዎችን ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርገው ግሎባል ፈንድ፤ በኬንያ የሚመረተውን ቲኤልዲ (የመጀመሪያ ተመራጭ የኤችአይቪ መድኃኒት) ለሞዛምቢክ አቅርቧል፡፡ አፍሪካ ሠራሹ ቲኤልዲ ወደ ፈንዱ አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ሲገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
የኬንያ ዩኒቨርሳል ኮርፖሬሽን በጎርጎሮሳውያኑ 2023 ለቲኤልዲ የዓለም ጤና ድርጅት ቅድመ-ምዘናን በማሟላት የመጀመሪያው የአፍሪካ አምራች ሆኗል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት የኤችአይቪ፣ “ሄፓታይተስ” እና የአባላዘር በሽታ በሽታዎች ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ሜግ ዶኸርቲ፤ እርምጃው የአፍሪካን የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት የሚያጠናከር እና ያልተቋረጠ የኤችአይቪ ሕክምናን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X