ሩሲያ ትብብርን ለማጠናከር በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን እዳ እንደምትሰርዝ አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ ትብብርን ለማጠናከር በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን እዳ እንደምትሰርዝ አስታወቀች
ሩሲያ ትብብርን ለማጠናከር በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን እዳ እንደምትሰርዝ አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.08.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ ትብብርን ለማጠናከር በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን እዳ እንደምትሰርዝ አስታወቀች

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ኮንስታንቲን ኮሳቼቭ፤ የሩሲያ የበጀት ሕግጋት ያልተከፈለ እዳ ላለባቸው ሀገራት ተጨማሪ ብድር መስጠት ወይም ከእነርሱ ጋር ትብብር ማድረግ እንደሚከለክል ገልፀዋል፡፡

ኮሳቼቭ አብዛኛው እዳ በቀድሞው ሶቪዬት ሕብረት ዘመን የተወሰደ ሲሆን ከርዕዮተ ዓለም አሰላለፍ ጋር በተያያዘ የማይመለስ ብድር ተደርጎ ይሰጥ እንደነበር አጽንኦዖት ሰጥተዋል፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት ግን ሩሲያ ለአፍሪካ ሀገራት ከ20 ቢሊየን ዶላር በላይ እዳ መሰረዟን ጠቅሰዋል፡፡

ሩሲያ እነዚህ ገንዘቦች በራሷ በጀት ውስጥ ቢኖሩላት ደስ እንደሚላት ባይሸሽጉም፤ አብዛኛዎቹ ባለእዳ ሀገራት እዳውን መክፈል ያለመቻላቸውን እውነታ ኮሳቼቭ አስታውሰዋል፡፡ ስለዚህ ለቀጠለው አጋርነት እና ለወደፊት ትብብር ሲባል የእዳ ስረዛ ተገቢ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0