ሩዋንዳ 250 የሚደርሱ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለመቀበል መስማማቷ እየተዘገበ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩዋንዳ 250 የሚደርሱ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለመቀበል መስማማቷ እየተዘገበ ነው
ሩዋንዳ 250 የሚደርሱ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለመቀበል መስማማቷ እየተዘገበ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.08.2025
ሰብስክራይብ

ሩዋንዳ 250 የሚደርሱ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለመቀበል መስማማቷ እየተዘገበ ነው

ውሉ በሩዋንዳ መንግሥት ቃል አቀባይ ዮላንዴ ማኮሎ ማረጋገጫ ማግኘቱን የምዕራባውያን የዜና ኢጀንሲ ዘግቧል፡፡ አሜሪካ ጀርባቸው የሚጠኑ የ10 ሰዎችን ዝርዝር መላኳ ተዘግቧል፡፡

የሩዋንዳ ውሳኔ "ዳግም ውህደት እና ማገገም" በሚሉ ማኅበራዊ እሴቶቿ ላይ የተመሠረተ ነው ያሉት ማኮሎ፤ ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ ፈቃድ ያገኙ ግለሰቦች የመኖሪያ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተናገረዋል፡፡

ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ወደ ሦስተኛ ሀገር የማጋዝ አማራጭን ስታስስ የነበረችው አሜሪካ፤ ለዚህ ፕሮግራም ለሩዋንዳ የገንዘብ ድጋፍ የምታደርግ ሲሆን ትክክለኛው የገንዘብ መጠን ግን አልተገለጸም፡፡ በዚህም መሠረት፦

ሩዋንዳ እያንዳንዱን ግለሰብ መርምራ የወንጀል ታሪክ የሌላቸውን ብቻ ትቀበላለች፡፡

ሕጻናት ላይ ወሲባዊ ጥቃት ፈጻሚዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

ስምምነቱ በጋራ መግባባት ሊራዘም ይችላል፡፡

ወደ ሩዋንዳ የሚላኩ ግለሰቦችም በሀገሪቱ እንዲቆዩ አይገደዱም፡፡

ሩዋንዳ ቀደም ሲል ከእንግሊዝ ጋር ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለማዛወር ያደረገችው ስምምነት ተቋርጧል፡፡ በወቅቱ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ንኮሳዛና ድላሚኒ-ዙማ ስምምነቱ "አዲስ ዓይነት የቅኝ ግዛት ብዝበዛ" እንደሆ በመግለጽ፤ የአፍሪካ ሀገራትን "ያልተፈለጉ ስደተኞች መጣያ" ሊያደርጋቸው እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0