ኢትዮጵያ እና ቱርክሜኒስታን ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉብት መንገድ ዙሪያ ተወያዩ
17:33 05.08.2025 (የተሻሻለ: 18:14 05.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ቱርክሜኒስታን ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉብት መንገድ ዙሪያ ተወያዩ
የኢትዮጵያ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ሥሜ ከቱርክሜኒስታን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አክመድ ጉርባኖቭ ጋር የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ሰለማሳደግ መክረዋል፡፡
ከሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት በማደግ ላይ ያሉ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን የተደረገው ውይይት፦
በትራንስፖርት፣
በዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ፣
በባሕል እና
በሰብዓዊ ጉዳዮች ትብብርን ማስፋት ላይ ያተኮረ ነበር።
◾ ሁለቱ ወገኖች ግንኙነቶችን በማጠናከር ለዘላቂ ልማት እና ለቀጣናዊ ውህደት የጋራ እርምጃዎችን ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ማረጋገጣቸውን የቱርክሜኒስታን ሚዲያ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ልዑካን በታህሳስ 2025 በቱርክሜኒስታን ሊካሄድ የታቀደውን ዓለም አቀፍ የሰላም እና መተማመን መድረክ እንደሚደግፍም ገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia