ኢኮዋስ “ኢኮ” የተሰኘ የመገበያያ ገንዘብ በ2027 አገልግሎት ላይ እንደሚያውል አስታወቀ
17:41 05.08.2025 (የተሻሻለ: 17:44 05.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢኮዋስ “ኢኮ” የተሰኘ የመገበያያ ገንዘብ በ2027 አገልግሎት ላይ እንደሚያውል አስታወቀ
የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው 'ኢኮ' ነጠላ መገበያያ ገንዘብ ሁሉም አባል ሀገራት ቢሳተፉም ባይሳተፉም በ2027 ይጀመራል ብሏል፡፡
የኢኮዋስ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኦማር አሊዩ ቱሬይ ከጋምቢያው ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው ጋር በነበራቸው ስብሰባ ላይ ይህን አረጋግጥዋል፡፡
መገበያያው ለቀጣናዊ የገንዘብ ውህደት ትልቅ እርምጃ እና ኢኮዋስ “ስትራቴጂያዊ ተለዋዋጭ” አካሄድን እየተከተለ እንደሆነ አመላክች ነው ተብሏል፡፡
ሁሉም አባል ሀገራት የውህደቱን መስፈርቶች እስኪያሟሉ ከመጠበቅ ይልቅ፤ ዝግጁ በሆኑ ሀገራት የመገበያያ ገንዘቡን በማሰጀመር ወደ ኋላ የቀሩትን ለመደገፍ ወጥኗል፡፡
ቱሬይ “የመገበያያ ገንዘቡ መጀመር አባል ሀገራት ማሟላት ያለባቸውን በርካታ መስፈርቶች የሚጠይቅ ሲሆን እስከሚጀመርበት ጊዜ ድረስ መስፈርቶቹ ይሟላሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ በባንጁል ለጋዜጠኞች ተናገረዋል፡፡
የ “ኢኮ” መገበያያ በውጭ ምንዛሬዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ፤ የበለጠ የተቀናጀ እና ሉዓላዊ የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ቀጣናን ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X