”በአዲስ አበባ በኩል ወደ ሞስኮ የምንሰጠውን አገልግሎት አጠናክረን እንቀጥላለን” - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈፃሚ

ሰብስክራይብ

”በአዲስ አበባ በኩል ወደ ሞስኮ የምንሰጠውን አገልግሎት አጠናክረን እንቀጥላለን” - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈፃሚ

አየር መንገዱ ከታህሳስ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሞስኮ በየቀኑ መብረር እንደሚጀምር ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ሞስኮ የሚደረገውን ሳምንታዊ በረራ በያዝነው ሐምሌ ወር ከአራት ወደ አምስት እንደሚያሳድግም ከዚህ በፊት ገልጿል፡፡

የአየር መንገዱ ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልከቶ ከሰጡት መግለጫ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ቃል ፍላጎቱ ካለ በቀን ሁለቴም በረራ ሊካሄድ የሚችልበት መንገድ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

“በአዲስ አበባ በኩል አድርገን ወደ ሞስኮ የምንወስዳቸው መንገደኞች ከአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ከብዙ አፍሪካ ሀገሮች የመጡ ናቸው። እና ይሄን አገልግሎት ስንጀምር በሶስት በረራ ነው የጀመርነው፡፡ ከዛ በኋላ የመንገደኛው ፍላጎት እያደገ ሲመጣ እኛም በረራችንን አሳድገን አሁን ያለበት ደረጃ ደርሷል። ወደ ሰባት እናሳድጋለን ስንል ፍላጎት ጨምሯል ማለት ነው። ስለዚህ መጀመሪያ ሰባት እናደርጋለን፤ ከዛ በኋላ ፍላጎቱ የበለጠ ካደገ በቀን ሁለቴም የምንሄድበት ሁኔታ አለ እና እኛ ደስተኞች ነን። ይሄንን በአዲስ አበባ በኩል ወደ ሞስኮ የምንሰጠውን አገልግሎት አጠናክረን እንቀጥላለን።”

አክለውም አየር መንገዱ በአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋራ በተሻለ ትብብር ለመስራት ዝግጁ እንደሆነ ግልፀዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0