አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ
15:39 05.08.2025 (የተሻሻለ: 15:44 05.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ
አምባሳደር ሱሌማን የሹመት ደብዳቤያቸውን ሐምሌ 28 ቀን 2017 በሞቃዲሾ ለሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሳላም ሀድሊዬ ዑመር አቅርበዋል፡፡ ተሿሚው አምባሰደር የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ነበረበት የመመለስ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግኑኝነት ታኅሣሥ 22 ቀን 2016 ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ ሻክሮ ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሞቃዲሾ በመጋቢት 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሐመድን አባራለች፡፡
◻ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም "የሁለቱን ሀገራት ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት አንድነትን ለማረጋገጥ” ያለመ በመርህ ላይ የተመሠረተ ስምምነት ላይ መድረሳቸውም የሚታወስ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X