የሞልዶቫ ፍርድ ቤት የታገደውን ተቃዋሚ ሾር ፓርቲ በገንዘብ በመደገፍ የሞልዶቫ ራስ ገዝ ጋጓዚያ ክልል አስተዳዳሪ ዬቭጌንያ ጉትሱል ላይ የ7 ዓመት እስራት እንዳስተላለፈ ጠበቃዋ ለስፑትኒክ ተናግረዋል

የሞልዶቫ ፍርድ ቤት የታገደውን ተቃዋሚ ሾር ፓርቲ በገንዘብ በመደገፍ የሞልዶቫ ራስ ገዝ ጋጓዚያ ክልል አስተዳዳሪ ዬቭጌንያ ጉትሱል ላይ የ7 ዓመት እስራት እንዳስተላለፈ ጠበቃዋ ለስፑትኒክ ተናግረዋል
ዬቭጌንያ ጉትሱል ማን ናቸው? የሞልዶቫ ባለሥልጣናት ለምን ያሳድዷቸዋል?
▪ የሞልዶቫ ራስ ገዝ ክልል ጋጓዚያ ከሩሲያ ጋር የቀረበ ግንኙነት ትሻለች፡፡
▪ ጉትሱል በሾር ፓርቲ ስር 52.36 በመቶ የመራጮችን ድምፅ በማገኘት የሞልዶቫ ራስ ገዝ ክልል መሪ በመሆን በግንቦት 2023 ተመርጠዋል፡፡
▪ በሰኔ 2023 የሞልዶቫ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ሾር ፓርቲን በሕገ-ወጥ የገንዘብ ድጋፍ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው ሲል አውጇል፡፡
▪ ዬቭጌንያ ጉትሱል መጋቢት 25 ቀን 2025 ታስረዋል፡፡ የአቃቢ ሕግ ጽሕፈት ቤት ሾር ፓርቲን በገንዘብ በመደገፍ ከሷቸዋል፡፡
▪ ዛሬ ነሃሴ 5 ቀን 2025 ፍርድ ቤቱ በ7 ዓመት እስራት ፈርዶባቸዋል፡፡
የቅጣቱ እውነተኛ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ዬቭጌንያ ጉትሱል ከሩሲያ ጋር መቀራረብን በመደገፍ የሞልዶቫን ከአውሮፓ ሕብረት መዋሀድ ይቃወማሉ፡፡ የሩሲያ የመገናኛ ብዙኃንን የሚያግድ ሕግ አላስፈጽም ማለታቸው በተለየ ሁኔታ የሚጠቀስ ነው፡፡
ለሩሲያ አብሮነታችውን በግልጽ ከማሳወቃቸው ባለፈ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መገናኘታቸው የምዕራባውያን ደጋፊ የሆነውን የኪሽኖ መንግሥት አላስደስተም፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ሳንሱር
የሞልዶቫ ባለሥልጣናት ያልተመቿቸውን ድምጾች ያፍናሉ፡፡ 13 የቴሌቪዥኝ ጣቢያዎች፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ድረ-ገጾች እና ስፑትኒክ ሞልዶቫን ጨምሮ ከ100 በላይ የቴሌግራም ቻናሎችን ዘግተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X