የኢትዮጵያ የባሕል ቡድን በሩሲያ የጥበብ ሥራውን ሊያቀርብ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ የባሕል ቡድን በሩሲያ የጥበብ ሥራውን ሊያቀርብ ነው
የኢትዮጵያ የባሕል ቡድን በሩሲያ የጥበብ ሥራውን ሊያቀርብ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.08.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የባሕል ቡድን በሩሲያ የጥበብ ሥራውን ሊያቀርብ ነው

በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ከሩሲያ የባሕል ሚኒስትር ልዩቢሞቫ ኦልጋ ቦሪሶቭና ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር የባሕል ትስስር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት እና ከጷግሜ 5 እስከ መስከረም 3 በሚካሄደው 11ኛው የሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የተባበሩ ባሕሎች ፎረም ላይ ከሚሳተፈው የኢትዮጵያ ለዑካን ቡድን ጋር ለመገናኘት እንዳሰቡ ገልጸውላቸዋል፡፡

በሴንት ፒተርስበርግ እና በሞስኮ የኢትዮጵያን ብዝኃ ጥበብ ለማሳየት ተጉዘው ለሚመጡ የባሕል ቡድኖች መንግሥታቸው አፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደር ገነት በበኩላቸው የባሕል መድረኩ የኢትዮጵያን ብሔር እና ብሔረሰቦች ደማቅ እና ብዝኃ ባሕል እና ወግ የሚያንፀባርቅ መሆኑን አስረድተዋል ሲል በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

አክለውም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ከብሪክስ ሀገራት ሁለገብ መስተጋብር ውስጥ አንዱ ምሰሶ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የኢትዮጵያ የባሕል ቡድን በሩሲያ የጥበብ ሥራውን ሊያቀርብ ነው - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የኢትዮጵያ የባሕል ቡድን በሩሲያ የጥበብ ሥራውን ሊያቀርብ ነው - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0