የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ19 ሚሊየን በላይ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ መንገደኞችን እንዳጓጓዘ ገለፀ
11:46 05.08.2025 (የተሻሻለ: 11:54 05.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ19 ሚሊየን በላይ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ መንገደኞችን እንዳጓጓዘ ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ19 ሚሊየን በላይ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ መንገደኞችን እንዳጓጓዘ ገለፀ
ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ11 በመቶ አድገት እንዳለው፤ አየር መንገዱ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጿል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች፦
አየር መንገዱ 7.6 ቢሊየን ዶላር ገቢ ሰብስቧል፣
ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ8 በመቶ ብልጫ አለው፣
ከ785 ሺህ ቶን በላይ ጭነት አጓጉዟል፣
13 ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው “አየር መንገዱ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ተወዳዳሪነቱን ማስቀጠል ችሏል” ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X