የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዶኔስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ አስተዳዳሪ ዴኒስ ፑሺሊን ሪፖርት ተቀበሉ
18:42 04.08.2025 (የተሻሻለ: 18:44 04.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዶኔስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ አስተዳዳሪ ዴኒስ ፑሺሊን ሪፖርት ተቀበሉ
ውይይቱ በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር፦
◾ መሠረተ ልማት እና መልሶ ግንባታ፦
በዚህ ዓመት በዶኔትስክ የግንባር ወረዳዎች109 ትምህርት ቤቶችን፣ 22 የስፖርት ማዕከላትን እና 57 የባሕል ማዕከሎችን ለማደስ ታቅዷል።
እ.ኤ.አ ከ2022 ጀምሮ 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር መንገዶች ታድሰዋል ወይም ተገንብተዋል፤ ተጨማሪ 800 ኪሎ ሜትር መንገዶችን ለመሥራት ታቅዷል።
◾ የውሃ አቅርቦት ችግር፦
በአሁኑ ጊዜ 60 በመቶ የሚሆነው ውሃ ባረጁ የቧንቧ መስመሮች ምክንያት እየባከነ ይገኛል።
ችግሩን ለመፍታት የውሃ ፍሳሾችን መጠገን እና የወንዝ ዳርቻዎችን ማጽዳት ሥራዎች እየተከናወኑ ሲሆን በየቀኑ ከ100 በላይ እንዲሁም በሳምንት እስከ 2 ሺህ የሚደርሱ ጥገናዎች እየተደረጉ ነው።
ከሞስኮ፣ ከሴንት ፒተርስበርግ እና ከሌሎች ደጋፊ ክልሎች 50 የጥገና ቡድኖች እና 148 የውሃ መኪናዎች ድጋፍ ተልኳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X