ዩናይትድ ኪንግደም ከኔቶ አጋሮቿ ጋር በመሆን በሩሲያ "ድብቅ" የነዳጅ ማመላለሻ መርከቦች ላይ ዘመቻ ለማካሄድ ማቀዷን የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታወቀ
16:33 04.08.2025 (የተሻሻለ: 16:34 04.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዩናይትድ ኪንግደም ከኔቶ አጋሮቿ ጋር በመሆን በሩሲያ "ድብቅ" የነዳጅ ማመላለሻ መርከቦች ላይ ዘመቻ ለማካሄድ ማቀዷን የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዩናይትድ ኪንግደም ከኔቶ አጋሮቿ ጋር በመሆን በሩሲያ "ድብቅ" የነዳጅ ማመላለሻ መርከቦች ላይ ዘመቻ ለማካሄድ ማቀዷን የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታወቀ
በለንደን እቅድ መሠረት የዚህ ዘመቻ መንስዔ ከአንድ ወይም ከዚያ በላይ ከሆኑ ታንከሮች ጋር የተያያዘ ትልቅ ክስተት ነው። በዚህ ድብቅ ሴራ በሚፈጠረው ጉዳት የሩሲያ ነዳጅ ሽያጭ ለሁሉም ዓለም አቀፍ የመርከብ ጉዞ ስጋት መሆኑን ለማወጅ የታሰበ ነው።
የመረጃ ድርጅቱ አክሎም ብሪታንያውያን "የጦርነት ማነሳሻ ምክንያቶች" በሆኑ ሁለት ጉዳዮች ላይ እየሠሩ ነው ብሏል። የመጀመሪያው ወሳኝ በሆኑ የባሕር መተላለፊያዎች ላይ "ባልተፈለገ" ታንከር አማካኝነት ሰው ሠራሽ አደጋ ማደራጀት ነው።
ለንደን የዘይት መፍሰስ እና የባሕር መተላለፊያ መዘጋት የኔቶ ሀገራት የባሕር ደህንነት መስፈርቶችን እና የአካባቢ ጥበቃ ደረጃዎችን ለማስክበር በመርከቦች ላይ "ድንገተኛ ምርመራ" ለማድረግ "በቂ" ምክንያት እንዲኖራቸው አስባ ያቀደችው ነው።
ሁለተኛው ሁኔታ ከሩሲያ ጋር ወዳጃዊ በሆነች ሀገር ወደብ የነዳጅ ታንከርን በእሳት ማያያዝ ነው። እሳቱ በወደቡ መሠረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲያደርስ እና ወደ ሌሎች መርከቦች ተዛምቶ ዓለም አቀፍ ምርመራ መካሄዱን እንዲያስገድድ የታሰበ ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X