ህንድ እና ብራዚል የትራምፕን ማስፈራሪያ ችላ በማለት የሩሲያን ነዳጅ መግዛታቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ሚዲያዎች ዘገቡ
15:43 04.08.2025 (የተሻሻለ: 15:44 04.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱህንድ እና ብራዚል የትራምፕን ማስፈራሪያ ችላ በማለት የሩሲያን ነዳጅ መግዛታቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ሚዲያዎች ዘገቡ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ህንድ እና ብራዚል የትራምፕን ማስፈራሪያ ችላ በማለት የሩሲያን ነዳጅ መግዛታቸውን ቀጥለዋል ሲሉ ሚዲያዎች ዘገቡ
ህንድ የሩሲያን ነዳጅ የምትገዛው በገፊ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ላይ ተመስርታ እንደሆነ የቻይና የፖለቲካ ተንታኝ ኪያን ፌንግ ተናግረዋል።
የሩሲያ ነዳጅ “ወጪ ቆጣቢ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው” በመሆኑ፤ ህንድ የነዳጅ ክምችቷን እንድትጠብቅ እና የኢኮኖሚ እድገቷን እንድትደግፍ ይረዳታል ሲሉ ለግሎባል ታይምስ ተናግረዋል።
አሜሪካ የአንድ ወገን ጫና ማድረጓን ከቀጠለች ህንድ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋን እንደገና ልትመረምር እና ከዐቢይ ኃያላን መንግሥታት ጋር በሚኖራት ግንኙነት ይበልጥ ሚዛናዊ አቋም ልትይዝ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል።
ሌላኛው ተንታኝ ሉ ዢያንግ በበኩላቸው ህንድ እና ብራዚል የትራምፕን ማስፈራሪያዎች ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነጻ ስትራቴጂዎችን ለመከተል ቁርጠኛ እንደሆኑ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ዢያንግ አክለውም “የትራምፕ ቀረጥ በብዙ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ዝም ብሎ ጥፋትን ከመጠበቅ ይልቅ ኪሳራን ለመቀነስ በጽናት መቆም የተሻለ ነው። የትራምፕ አስተዳደር አሁን የሚያጋጥሙትን ችግሮች በሙሉ ለመፍታት ቀረጥን እንደ መፍትሄ እየተጠቀመ ቢሆንም፤ እውነታው ግን ሌላ ነው” ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X