በአውሮፓ ሕብረት ተከልክለው የአውሮፓ ኩባንያዎች በምሥራቅ አፍሪካ የሚልኳቸው ፀረ-ተባዮች፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ንቦችን እየገደሉ እና የሥነ-ምህዳር ስርዓቱን እያናጉ እንደሆነ ተነገረ

በአውሮፓ ሕብረት ተከልክለው የአውሮፓ ኩባንያዎች በምሥራቅ አፍሪካ የሚልኳቸው ፀረ-ተባዮች፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ንቦችን እየገደሉ እና የሥነ-ምህዳር ስርዓቱን እያናጉ እንደሆነ ተነገረ
ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች በንቦች ላይ ባደረሱት ጥፋት ምክንያት በሩዋንዳ የማር ምርት በእጅጉ እንደተጎዳ እና የብዙ ንብ አርቢ ቤተሰቦች ኑሮ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ተመራማሪዎችን ጠቅሶ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
ረዘም ያለ ዝናብ አንድ ምክንያት ቢሆንም በተለይም በኡጋንዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ እና ኬንያ ለንቦች መሞት ዋና መንስኤዎች የፀረ-ተባይ መድኃኒቶች ናቸው። ንቦች ግብርና ለሀገር ውስጥ ምርት እና ለሥራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በሚያደረግበት ክልል ውስጥ ለዋና ዋና ሰብሎች የዘር ስርጭት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡
ሩዋንዳ የተፈጥሮ ፒሬትረም ፀረ-ተባይ መድኃኒት ምርቷን ወደ ውጭ በመላክ፤ ሰው ሠራሽ አማራጮችን ታስመጣለች፦
▪72 በመቶ የሚሆኑ አርሶ አደሮች ለንቦች መርዛማ የሆነውን ሮኬት የተባለ ፀረ-ተባይ መድኃኒት ይጠቀማሉ።
▪22 በመቶ የሚሆኑት ማላቲዮን የተባለውን መድኃኒት ይጠቀማሉ።
ማላቲዮን በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ የተከለከለ ቢሆንም፤ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ወደ ሩዋንዳ መላካቸውን እንደቀጠሉ የአውሮፓ ኬሚካሎች ኤጀንሲ አስታውቋል።
እ.ኤ.አ በ2022 የአውሮፓ ሕብረት ሀገራት ከ81 ሺህ ቶን በላይ የሚሆኑ በሕብረቱ ውስጥ የተከለከሉ 41 ዓይነት ፀረ-ተባይ መድኃኒቶችን ለውጭ ሀገራት ልከዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X