ኢትዮጵያ ከስጋና የእርድ ተረፈ ምርቶች 120 ሚሊየን ዶላር ገቢ ሰበሰበች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ከስጋና የእርድ ተረፈ ምርቶች 120 ሚሊየን ዶላር ገቢ ሰበሰበች
ኢትዮጵያ ከስጋና የእርድ ተረፈ ምርቶች 120 ሚሊየን ዶላር ገቢ ሰበሰበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.08.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከስጋና የእርድ ተረፈ ምርቶች 120 ሚሊየን ዶላር ገቢ ሰበሰበች

የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ባከናወናቸው በርካታ ሥራዎች የተገኘ ውጤት እንደሆነ አስታውቋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አስራት ጤራ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከስጋ በተጨማሪ ኩላሊት፣ ጉበት እና ምላስን ጨምሮ 21 አይነት የተረፈ ምርቶችን ወደ ውጭ እንደምትልክ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በጠናቀቀው በጀት ዓመት 22 ሺህ 620 ቶን የእንስሳት ተረፈ ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 120 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

ይህ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ53 በመቶ ጭማሪ አለው።

ስጋ እና የስጋ ተረፈ ምርቶች በስፋት ለገበያ ከቀረቡባቸው የዓለም ሀገራት መካከል ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች እንደሆኑ ማርና ሰም ደግሞ እንደ  ጃፓን፣ ጀርመን እና አሜሪካ ባሉ ሀገሮች ተልከዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0