ኢትዮጵያና ቻይና የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን ለማዘመን ንግግር ጀመሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያና ቻይና የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን ለማዘመን ንግግር ጀመሩ
ኢትዮጵያና ቻይና የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን ለማዘመን ንግግር ጀመሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.08.2025
ሰብስክራይብ

 ኢትዮጵያና ቻይና የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመርን ለማዘመን ንግግር ጀመሩ

760 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውን የባቡር መስመር ማሻሻል ካስፈለገባቸው ምክንያቶች አንዱ በየጊዜው የሚከሰተው የከብቶች አደጋ ነው።

ይህም በባቡር መስመሩ አካባቢ ከሚኖሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰቦች ጋር ተደጋጋሚ ውዝግብ እና ግጭት እንደፈጠረ  የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል።

የመሠረተ ልማት ማሻሻያው ተጨማሪ ድልድዮችን፣ አጥሮችን እና የእንስሳት መሻገሪያዎችን መገንባት እንዲሁም ተጨማሪ ሎኮሞቲቮችን መግዛት እንደሚያካትት የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ዘግቧል።

ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ "የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ተጨማሪ ፋይናንስ ያስፈልገዋል። ይህ ከቻይና መንግሥት ጋር በቅርቡ ውይይት ካደረግንባቸው ጉዳዮች አንዱ ነበር። የባቡር መስመሩ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ተስማምተናል" ሲሉ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር 'የባቡር መሠረተ ልማት ለንግድና ቀጣናዊ ትስስር' በሚል መሪ ሃሳብ ባካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0