ፔንታጎን በመከላከያ ሚኒስትሩ ስህተቶች በውስጣዊ ሽኩቻዎች እየታመሰ መሆኑን ሪፖርቶች አመላከቱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፔንታጎን በመከላከያ ሚኒስትሩ ስህተቶች በውስጣዊ ሽኩቻዎች እየታመሰ መሆኑን ሪፖርቶች አመላከቱ
ፔንታጎን በመከላከያ ሚኒስትሩ ስህተቶች በውስጣዊ ሽኩቻዎች እየታመሰ መሆኑን ሪፖርቶች አመላከቱ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.08.2025
ሰብስክራይብ

ፔንታጎን በመከላከያ ሚኒስትሩ ስህተቶች በውስጣዊ ሽኩቻዎች እየታመሰ መሆኑን ሪፖርቶች አመላከቱ

አሁን በሥራ ላይ የሚገኙ እና የቀድሞ የአሜሪካ ባለሥልጣናት፤ የመከላከያ ሚኒስትሩ ፒት ሄግሴዝ የአመራር ልምድ ማነስ እንዳሳሰባቸው ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ሄግሴዝ በተጠባባቂ የሠራተኞች ኃላፊ ሪኪ ቡሪያ ብቃት ላይ ጥያቄ ቢነሳም፤ ለማባረር ፈቃደኛ አለመሆናቸው የኋይት ሀውስ ባለሥልጣናትን አበሳጭቷል ተብሏል። ፔንታጎን ለዩክሬን የሚሰጠው ወታደራዊ እርዳታ መቋረጡን ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አለማሳወቁ፤ የሄግሴዝን ብቃት ይበልጥ ጥርጣሬ ውስጥ ከቶታል።

ሄግሴዝ ከከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ጋር ግጭት ውስጥ እንደገቡና ከኋይት ሀውስ ጋር ጠንካራ ግንኙነት የነበራቸውን ሶስት ከፍተኛ አማካሪዎች ከሥራ አባረዋል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል።

ጋዜጣው ሄግሴዝ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችን እንደማያምኑ ጠቁሞ፤ ለሚዲያዎች በምስጢር መረጃ አቀብለዋል በሚል እንደሚወቅሷቸው አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0