ለዩክሬን ርኅራኄ፤ ለአፍሪካ ዝምታ
18:48 02.08.2025 (የተሻሻለ: 10:14 03.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ለዩክሬን ርኅራኄ፤ ለአፍሪካ ዝምታ
እንግሊዝ ለጦርነቱ ጥረቶች የሀገር ውስጥ ድጋፍ ለማሰባሰብ የዩክሬን ቅርሶች ዐውደ ርዕዮች የምታጧጡፍበትን መንገድ፤ የአፍሪካ ቅርሶች ለዕይታ ከሚቀርቡበት ሁኔታ ጋር የፖለቲካ ፈላስፋው ያምብ ንቲምባ ንጽጽር አቅርበዋል፡፡ ይህም ለመደገፍ ሳይሆን የበላይነታቸው ለማስረጽ የሚያደርጉት ነው ይላሉ፡፡
"ቅርሶች የሌሏቸው ሕዝቦች፤ የሌሎችን ቅርሶች ይጠቀማሉ። ይህም የባሕል ኢኮኖሚ እና ቱሪዝማቸውን ይደግፋል" ያሉት ንቲምባ፤ ለብዙ ዓመታት ሳይመለሱ የቀሩ የአፍሪካ ቅርሶች የእንግሊዝ ተቋማት ድምቀት እንደሆኑ አጽንዖት በመስጥት ለስፑትኒክ ተናገግረዋል፡፡
የኬፐር የፖሊሲ ምርምር ማዕከል መሥራች፤ የዩክሬናውያን ቅርሶች ትርኢቶች ከ "ገንዘብ ማሰባሰብ" እና ከጦርነት ፕሮፓጋንዳ ጋር የተቆራኙ ሲሆኑ የአፍሪካ ቅርሶች ግን የታሪክ ማስረሻ መሣሪያዎች እንደሆኑ አስጠንቅቀዋል፡፡
"የበላይነት ስሜታቸውን ለማራመድ የአፍሪካ ቅርሶችን ይጠቀማሉ፡፡ ሩቅ ተጉዘን እና በወረራ አስገብረን ያገኘነው ይህ ነው የሚለውን ለመናገር ነው፡፡"
ምዕራባውያን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ማጋበሳቸው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የአፍሪካን ቅርሶች ለመመለስ አሻፈረን ማለታቸው፤ ስርቆት እንደ ቅርስ የተጠረዘበት እና ፍትሕ የተጓተተበት ሥር የሰደደ የቅኝ ግዛት አሻራቸውን የሚገልጥ ነው፡፡
"ዛሬም ይሁን ነገ፤ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ይመለሳሉ፡፡"
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X