የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰበ እና የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ቀውስ ለመግታት ቀጣናዊ የሰላም ጥረቶችን ለማስተባበር ተስማሙ
18:00 02.08.2025 (የተሻሻለ: 18:04 02.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰበ እና የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ቀውስ ለመግታት ቀጣናዊ የሰላም ጥረቶችን ለማስተባበር ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰበ እና የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ቀውስ ለመግታት ቀጣናዊ የሰላም ጥረቶችን ለማስተባበር ተስማሙ
የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ ሊቀ መንበር ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እና የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር ዊሊያም ሩቶ፤ የምስራቅ ኮንጎን ሰላም ለማጠናከር በናይሮቢ የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ማካሄዳቸውን የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
የስብሰባው ቁልፍ ውጤቶች፦
🟠 የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን፣ የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ እና የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰበ የቴክኒክ ጽሕፈት ቤቶቻቸውን በአፍሪካ ኅብረት አመራር ስር ያዋህዳሉ፡።
🟠 የሦስቱን ተቋማት ጥረቶች ወደ አንድ በማምጣት ለአፍሪካ መር ሰላም ይሠራሉ፡፡
🟠 አምስት የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎች በሰላም አመቻቸነት ተመርጠዋል፡፡
🟠 የናይሮቢ እና የሉዋንዳ ሂደቶች ይጣመራሉ፡፡
🟠 የገንዘብ ድጋፍ እና ቅንጅትን በተመለከተ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ይወያያሉ፡፡
የኬንያ ፕሬዝዳንት "የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መረጋጋት ለመካከለኛው አፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለመላው አሕጉራችን ሰላምና ኢኮኖሚያዊ እድገትም ወሳኝ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ምናንጋግዋ በበኩላቸው፤ "በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚገኙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ዘላቂ ሰላም እና ብሔራዊ አንድነት እንዲያገኙ ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
