ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ የኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ ለመጀመር ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ የኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ ለመጀመር ተስማሙ
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ የኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ ለመጀመር ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.08.2025
ሰብስክራይብ

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ የኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ ለመጀመር ተስማሙ

ሀገራቱ ሰኔ 27 ቀን በፈረሙት የሰላም ስምምነት መሠረት፤ የቀጣናዊ ኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ መርሆዎች ላይ መገባባታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

ሀገራቱ በኃይል፣ በመሠረተ ልማት፣ በማዕድን ቁፋሮ፣ በብሔራዊ ፓርክ አስተዳደር፣ በቱሪዝም እና በሕብረተሰብ ጤና በመተባበር በምሥራቅ እና በመካከለኛው አፍሪካ ቀጣና የኢኮኖሚ እድገትን ያፋጥናሉ ሲል መግለጫው አመላክቷል፡፡

የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ተቆጣጣሪ የጋራ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባን ተከትሎ ባወጣው መገለጫ፤ "የደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማስቀጠል ትርጉም ያላቸው እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው" ብሏል፡፡ 

በሳምንቱ ዋሽንግተን ላይ የተደረጉ ስብሰባዎች ዓላማዎች፦

🟠 በደህንነት ጉዳዮች ቅንጅትን ማጠናከር፣

🟠 የረጅም ጊዜ መረጋጋት እና ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ፣

🟠 በቀጣናው ያለውን "የላቀ ኢኮኖሚያዊ አቅም" ማውጣት፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ የኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ ለመጀመር ተስማሙ
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሩዋንዳ የኢኮኖሚ ውህደት ማዕቀፍ ለመጀመር ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.08.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0