የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የወጪ ንግድ ገቢ ቢቀንስም የገቢ እቅዱን 99 በመቶ እንዳሳካ አስታወቀ
17:11 02.08.2025 (የተሻሻለ: 20:24 02.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የወጪ ንግድ ገቢ ቢቀንስም የገቢ እቅዱን 99 በመቶ እንዳሳካ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የወጪ ንግድ ገቢ ቢቀንስም የገቢ እቅዱን 99 በመቶ እንዳሳካ አስታወቀ
ኮርፖሬሽኑ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል የተባለ ሲሆን ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ማደጉ ተነግሯል፡፡ ከወጪ ንግድ ለማግኘት ካስቀመጠው 146 ሚሊየን ዶላር ገቢ፤ በ15 በመቶ ያነሰ 124 ሚሊየን ዶላር ማሳካቱን ነው የገለፀው፡፡
በተኪ ምርት እንቅስቃሴ በበጀት ዓመቱ 18 ቢሊየን ብር የሚገመት ምርት ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 11 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ሁለት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ መመረታቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ፍሰሃ ይታገሱ ለሚዲያዎች በሰጡት ገለጻ አመላክተዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ፦
14 ቢሊዮን ብር የገበያ ትስስሮች ተፈጥረዋል፡፡
48 ሺህ 900 አዲስ የሥራ እድል ተፈጥሯል፡፡
ከ80 በላይ አዳዲስ ኩባንያዎች ፓርኮቹን ተቀላቅለዋል፡፡
የኢንቨስትመንት ፍሰቱ አንድ ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
ℹ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ አምራቾች፣ የመኪና መገጣጠሚያዎች፣ የቡና እና የማር ማቀነባበሪያዎች የኮርፖሬሽኑን የገቢ ምንጭ የጨመሩ አዳዲስ አምራቾች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X